ምሳሌ 16:24-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. ደስ የሚያሰኝ ቃል የማር ወለላ ነው፤ለነፍስ ጣፋጭ፣ ለዐጥንትም ፈውስ ነው።

25. ለሰው ቀና መስሎ የሚታይ መንገድ አለ፤በመጨረሻ ግን ወደ ሞት ይመራል፤

26. ሠራተኛን የዕለት ጒርስ ፍላጎቱ ታታሪ ያደርገዋል፤ራቡም ይገፋፋዋል።

27. ወራዳ ሰው ክፋትን ያውጠነጥናል፤ንግግሩም እንደሚለበልብ እሳት ነው።

28. ጠማማ ሰው ጠብን ይዘራል፤ሐሜተኛም የቅርብ ወዳጆችን ይለያያል።

ምሳሌ 16