24. ወደ ሲኦል ከመውረድ እንዲድን፣የሕይወት መንገድ ጠቢቡን ሰው ወደ ላይ ትመራዋለች።
25. እግዚአብሔር የትዕቢተኛውን ቤት ያፈርሰዋል፤የመበለቲቱን ዳር ድንበር ግን እንዳይደፈር ይጠብቃል።
26. እግዚአብሔር የክፉውን ሰው ሐሳብ ይጸየፋል፤የንጹሓን ሐሳብ ግን ደስ ያሰኘዋል።
27. ስስታም ሰው በቤተ ሰቡ ላይ ችግር ያመጣል፤ጒቦን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል።
28. የጻድቅ ሰው ልብ የሚሰጠውን መልስ ያመዛዝናል፤የክፉ ሰው አፍ ግን ክፋትን ያጐርፋል።