ምሳሌ 15:18-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. ግልፍተኛ ሰው ጠብ ያነሣሣል፤ታጋሽ ሰው ግን ጠብን ያበርዳል።

19. የሀኬተኛ መንገድ በእሾህ የታጠረች ናት፤የቅኖች መንገድ ግን የተጠረገ አውራ ጐዳና ነው።

20. ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ተላላ ሰው ግን እናቱን ይንቃል።

ምሳሌ 15