ምሳሌ 15:14-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. አስተዋይ ልብ ዕውቀትን ይሻል፤የተላላ አፍ ግን ቂልነትን ያመነዥካል።

15. የተጨቈኑ ሰዎች ዘመናቸው ሁሉ የከፋ ነው፤በደስታ የተሞላ ልብ ግን የማይቋረጥ ፈንጠዝያ አለው።

16. እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋር ያለ ጥቂት ነገር፣ሁከት ካለበት ትልቅ ሀብት ይበልጣል።

17. ፍቅር ባለበት ጐመን መብላት፣ጥላቻ ባለበት የሰባ ፍሪዳ ከመብላት ይሻላል።

ምሳሌ 15