ምሳሌ 15:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የለዘበ መልስ ቊጣን ያበርዳል፤ክፉ ቃል ግን ቊጣን ይጭራል።

2. የጠቢብ አንደበት ዕውቀትን ታወድሳለች፤የተላሎች አንደበት ግን ቂልነትን ያፈልቃል።

3. የእግዚአብሔር ዐይኖች በሁሉም ስፍራ ናቸው፤ክፉዎችንም ደጎችንም ነቅተው ይመለከታሉ።

4. ፈውስ የምታመጣ ምላስ የሕይወት ዛፍ ናት፤አታላይ ምላስ ግን መንፈስን ትሰብራለች።

5. ተላላ የአባቱን ምክር ይንቃል፤መታረምን የሚቀበል ግን አስተዋይነቱን ያሳያል።

6. የጻድቃን ቤት በብዙ ሀብት የተሞላ ነው፤የክፉዎች ገቢ ግን መከራን ታመጣባቸዋለች።

7. የጠቢባን ከንፈር ዕውቀትን ታስፋፋለች፤የተላሎች ልብ ግን እንዲህ አይደለም።

ምሳሌ 15