ምሳሌ 15:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የለዘበ መልስ ቊጣን ያበርዳል፤ክፉ ቃል ግን ቊጣን ይጭራል።

2. የጠቢብ አንደበት ዕውቀትን ታወድሳለች፤የተላሎች አንደበት ግን ቂልነትን ያፈልቃል።

3. የእግዚአብሔር ዐይኖች በሁሉም ስፍራ ናቸው፤ክፉዎችንም ደጎችንም ነቅተው ይመለከታሉ።

ምሳሌ 15