ምሳሌ 14:5-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ታማኝ ምስክር አይዋሽም፤ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸትን ይዘከዝካል።

6. ፌዘኛ ጥበብን ይሻል፤ ሆኖም አያገኛትም፤ዕውቀት ግን ለአስተዋዮች በቀላሉ ትገኛለች።

7. ከተላላ ሰው ራቅ፤ከከንፈሮቹ ዕውቀት አታገኝምና።

8. የአስተዋዮች ጥበብ መንገዳቸውን ልብ ማለት ነው፤የተላሎች ሞኝነት ግን መታለል ነው።

9. ተላሎች በሚያቀርቡት የበደል ካሳ ያፌዛሉ፤በቅኖች መካከል ግን በጎ ፈቃድ ትገኛለች።

10. እያንዳንዱ ልብ የራሱን መራራ ሐዘን ያውቃል፤ደስታውንም ማንም ሊጋራው አይችልም።

11. የክፉዎች ቤት ይፈርሳል፤የቅኖች ድንኳን ግን ይስፋፋል።

ምሳሌ 14