ምሳሌ 14:15-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ተላላ ሰው ሁሉን ያምናል፤አስተዋይ ግን ርምጃውን ያስተውላል።

16. ጠቢብ ሰው ጥንቁቅ ነው፤ ከክፉም ይርቃል፤ተላላ ግን ችኵልና ደንታ ቢስ ነው።

17. ግልፍተኛ ሰው የቂል ተግባር ይፈጽማል፤መሠሪም ሰው አይወደድም።

18. ብስለት የሌላቸው ተላላነትን ይወርሳሉ፤አስተዋዮች ግን ዕውቀትን እንደ ዘውድ ይጭናሉ።

19. ክፉዎች በደጎች ፊት፣ኀጥኣንም በጻድቃን ደጅ ያጐነብሳሉ።

ምሳሌ 14