ምሳሌ 14:10-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. እያንዳንዱ ልብ የራሱን መራራ ሐዘን ያውቃል፤ደስታውንም ማንም ሊጋራው አይችልም።

11. የክፉዎች ቤት ይፈርሳል፤የቅኖች ድንኳን ግን ይስፋፋል።

12. ለሰው ቀና መስሎ የሚታይ መንገድ አለ፤በመጨረሻ ግን ወደ ሞት ያደርሳል።

13. በሣቅ ጊዜ እንኳ ልብ ይተክዛል፤ደስታም በሐዘን ሊፈጸም ይችላል።

ምሳሌ 14