ምሳሌ 13:7-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ምንም ሳይኖረው ባለጠጋ መስሎ የሚታይ ሰው አለ፤ሌላው ድኻ መስሎ ይታያል፤ ግን ብዙ ሀብት አለው።

8. የሰው ሀብቱ ለሕይወቱ ቤዛ ሊሆነው ይችላል፤ድኻው ግን ሥጋት የለበትም።

9. የጻድቃን ብርሃን ደምቆ ይበራል፤የክፉዎች መብራት ግን ይጠፋል።

10. ትዕቢት ጠብን ብቻ ያስፋፋል፤ጥበብ ግን ምክርን በሚቀበሉ ዘንድ ትገኛለች።

ምሳሌ 13