ምሳሌ 13:3-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. አንደበቱን የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል፤አፉ እንዳመጣለት የሚናገር ግን ይጠፋል።

4. ሰነፍ አጥብቆ ይመኛል፤ አንዳችም አያገኝም፤የትጉዎች ምኞት ግን ይረካል።

5. ጻድቅ ሐሰትን ይጠላል፤ክፉ ሰው ግን ኀፍረትንና ውርደትን ያመጣል።

6. ጽድቅ ቅን የሆነውን ሰው ትጠብቀዋለች፤ክፋት ግን ኀጢአተኛውን ትጥለዋለች።

7. ምንም ሳይኖረው ባለጠጋ መስሎ የሚታይ ሰው አለ፤ሌላው ድኻ መስሎ ይታያል፤ ግን ብዙ ሀብት አለው።

8. የሰው ሀብቱ ለሕይወቱ ቤዛ ሊሆነው ይችላል፤ድኻው ግን ሥጋት የለበትም።

ምሳሌ 13