ምሳሌ 13:22-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. ደግ ሰው ለልጅ ልጆቹ ውርስ ትቶ ያልፋል፤የኀጢአተኞች ሀብት ግን ለጻድቃን ይከማቻል።

23. የድኾች ዕርሻ የተትረፈረፈ ምርት ያስገኛል፤የፍትሕ መጓደል ግን ጠራርጎ ይወስደዋል።

24. በአርጩሜ ከመቅጣት የሚሳሳለት ልጁን ይጠላል፤የሚወደው ግን በጥንቃቄ ይቀጣዋል።

ምሳሌ 13