ምሳሌ 11:15-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ለማይታወቅ ሰው ዋስ የሚሆን መከራ ያገኘዋል፤ዋስትና ለመስጠት እጅ የማይመታ ግን ምንም አይደርስበትም።

16. ርኅሩኅ ሴት ክብር ታገኛለች፤ጒልበተኛ ሰዎች ግን ብልጽግናን ብቻ ያገኛሉ።

17. ደግ ሰው ራሱን ይጠቅማል፤ጨካኝ ግን በራሱ ላይ መከራ ያመጣል።

18. ክፉ ሰው የሚያገኘው ትርፍ መቅኖ የለውም፤ጽድቅን የሚዘራ ግን አስተማማኝ ዋጋ ያገኛል።

19. እውነተኛ ጻድቅ ሕይወትን ያገኛል፤ክፋትን የሚከተል ግን ወደ ሞቱ ይጓዛል።

20. እግዚአብሔር ልበ ጠማሞችን ይጸየፋል፤በመንገዳቸው ነቀፋ በሌለባቸው ሰዎች ግን ደስ ይሰኛል።

21. ክፉ ሳይቀጣ እንደማይቀር ዕወቅ፣ጻድቃን ግን በነጻ ይሄዳሉ።

22. በእርያ አፍንጫ ላይ እንደ ተሰካ የወርቅ ቀለበት፣ማስተዋል የጐደላት ቆንጆ ሴት እንዲሁ ናት።

23. የጻድቃን ምኞት ምንጊዜም ፍጻሜው ያማረ ነው፤የክፉዎች ተስፋ ግን በቊጣ ያከትማል።

24. አንዱ በለጋስነት ይሰጣል፤ ሆኖም ይበልጥ ያገኛል፤ሌላው ያለ መጠን ይሰስታል፤ ግን ይደኸያል።

ምሳሌ 11