ምሳሌ 11:12-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ማመዛዘን የጐደለው ሰው ባልንጀራውን ያንኳስሳል፤አስተዋይ ግን አንደበቱን ይገዛል።

13. ሐሜተኛ ምስጢር አይጠብቅም፤ታማኝ ሰው ግን ምስጢር ይጠብቃል።

14. በአመራር ጒድለት መንግሥት ይወድቃል፤የመካሮች ብዛት ግን ድልን ርግጠኛ ያደርጋል።

ምሳሌ 11