ምሳሌ 10:19-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. ከቃላት ብዛት ኀጢአት አይታጣም፤አንደበቱን የሚገታ ግን ጠቢብ ነው።

20. የጻድቅ አንደበት የነጠረ ብር ነው፤የክፉ ሰው ልብ ግን ርባና የለውም።

21. የጻድቃን ከንፈሮች ብዙዎችን ያንጻሉ፤ተላሎች ግን ከማመዛዘን ጒድለት ይሞታሉ።

22. የእግዚአብሔር በረከት ብልጽግናን ታመጣለች፤መከራንም አያክልባትም።

23. ተላላ ሰው በክፉ ተግባር ይደሰታል፤አስተዋይ ሰው ግን በጥበብ ደስ ይለዋል።

ምሳሌ 10