ምሳሌ 10:12-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ጥላቻ ጠብን ያነሣሣል፤ፍቅር ግን ስሕተትን ሁሉ ይሸፍናል።

13. ጥበብ በአስተዋይ ሰው ከንፈር ትገኛለች፤በትር ግን ማመዛዘን ለጐደለው ሰው ጀርባ ነው።

14. ጠቢባን ዕውቀት ያከማቻሉ፤የተላላ አንደበት ግን ጥፋትን ይጋብዛል።

15. የባለጠጎች ሀብት የተመሸገ ከተማቸው ነው፤ድኽነት ግን የድኾች መጥፊያ ናት።

ምሳሌ 10