ምሳሌ 1:6-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ይህም የጠቢባንን ምሳሌዎችንና ተምሳሌቶችን፣አባባሎችንና ዕንቆቅልሾችን ይረዱ ዘንድ ነው።

7. እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፤ተላሎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።

8. ልጄ ሆይ፤ የአባትህን ምክር አድምጥ፤የእናትህንም ትምህርት አትተው።

9. ለራስህ ሞገስን የሚያጐናጽፍ አክሊል፣ዐንገትህን የሚያስውብ ድሪ ይሆንልሃል።

10. ልጄ ሆይ፤ ኀጢአተኞች ቢያባብሉህ፣እሺ አትበላቸው፤

11. “ከእኛ ጋር ናና፣ ደም ለማፍሰስ እናድባ፤በደል በሌለበት ሰው ላይ እንሸምቅ፤

ምሳሌ 1