ምሳሌ 1:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ጥበብንና ተግሣጽን ለመቀበል፤ጥልቅ ሐሳብ የሚገልጡ ቃላትን ለማስተዋል፤

3. ጽድቅን፣ ፍትሕንና ሚዛናዊ ብያኔን በማድረግ፣የተገራ ጠቢብ ልቦናን ለማግኘት፤

4. ብስለት ለሌላቸው አስተዋይነትን፣በዕድሜ ለጋ ለሆኑት ዕውቀትንና ልባምነትን ለመስጠት፤

5. ጥበበኞች ያድምጡ፤ ትምህርታቸውንም ያዳብሩ፤አስተዋዮችም መመሪያ ያግኙበት፤

ምሳሌ 1