6. “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ ራስህን ወደ መሬት ወርውር፤ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአልና፤“ ‘እግርህ በድንጋይ እንዳይሰናከል፣በእጃቸው ያነሡህ ዘንድ፣መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል።’ ”
7. ኢየሱስም፣ “እንደዚሁም በመጻሕፍት፣ ‘እግዚአብሔር አምላክህን አትፈታተነው’ ተብሎ ተጽፎአል” በማለት መለሰለት።
8. እንደ ገናም ዲያብሎስ ኢየሱስን እጅግ ከፍ ወዳለ ተራራ አወጣው፤ የዓለምንም መንግሥታት ከነክብራቸው አሳየውና፣