ማቴዎስ 3:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በዚያን ወራት መጥምቁ ዮሐንስ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ።

2. ስብከቱም፣ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሓ ግቡ” የሚል ነበር።

3. በነቢዩ በኢሳይያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረለት እርሱ ነው፤“በምድረ በዳ፣‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ጎዳናውንም አስተካክሉ’ እያለ የሚጮህ ድምፅ።”

4. የዮሐንስ ልብስ የግመል ጠጕር ሲሆን፣ ወገቡንም በጠፍር ይታጠቅ ነበር። ምግቡም አንበጣና የበረሃ ማር ነበር።

ማቴዎስ 3