ማቴዎስ 22:33-37 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

33. ሕዝቡም ይህን በሰሙ ጊዜ በትምህርቱ ተደነቁ።

34. ኢየሱስ ሰዱቃውያንን ዝም እንዳሰኛቸው ሰምተው፣ ፈሪሳውያን በአንድነት ተሰበሰቡ፤

35. ከእነርሱም አንድ የኦሪት ሕግ አዋቂ፣ ሊፈትነው ፈልጎ እንዲህ አለው፤

36. “መምህር ሆይ፤ ከሕግ ሁሉ የሚበልጠው የትኛው ትእዛዝ ነው?”

37. እርሱም እንዲህ አለው፤ “ ‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ሐሳብህ ውደድ፤’

ማቴዎስ 22