2. እንዲህ አላቸው “ባቅራቢያችሁ ወዳለው መንደር ሂዱ፤ እንደ ደረሳችሁም አንዲት አህያ ከነውርንጫዋ ታስራ ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁም ወደ እኔ አምጧቸው።
3. ማንም ሰው ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ ቢላችሁ፣ ‘ጌታ ይፈልጋቸዋል’ በሉት፤ ወዲያውኑ ይሰዳቸዋል።”
4. ይህ የሆነውም በነቢዩ እንዲህ በማለት የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ነው።
5. “ለጽዮን ልጅ እንዲህ በሏት፤‘እነሆ፤ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ፣በአህያዪቱና በግልገሏ፣በውርንጫዪቱም ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።’ ”
6. ደቀ መዛሙርቱም ሄደው ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ።