ማቴዎስ 14:6-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ሄሮድስ የልደቱን ቀን ሲያከብር፣ የሄሮድያዳ ልጅ በዘፈን ደስ ስላሰኘችው፣

7. የምትጠይቀውን ሁሉ ሊሰጣት በመሓላ ቃል ገባላት።

8. ልጅቷም በእናቷ ተመክራ፣ “የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በሳሕን ላይ አድርገህ አሁኑኑ ስጠኝ” አለችው።

9. በዚህ ጊዜ ንጉሡ አዘነ፤ ይሁን እንጂ ስለ መሐላውና ከእርሱ ጋር ስለ ነበሩ እንግዶች ሲል ጥያቄዋ እንዲፈጸምላት አዘዘ።

10. ልኮም በወህኒ ውስጥ እንዳለ የዮሐንስን ራስ አስቈረጠ።

11. የተቈረጠውንም ራስ በሳሕን ላይ አድርገው ለልጅቱ ሰጧት፤ ልጅቱም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች።

ማቴዎስ 14