ማቴዎስ 14:15-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. እየመሸ በመሄዱም ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው፣ “ይህ ስፍራ ምንም የማይገኝበት ምድረ በዳ ነው፤ ጊዜው እየመሸ ስለ ሆነ፣ ወደ መንደሮች ሄደው የሚበሉት ምግብ እንዲገዙ ሕዝቡን አሰናብት” አሉት።

16. ኢየሱስ ግን፣ “መሄድ አያስፈልጋቸውም፤ የሚበሉትን እናንተ ስጧቸው” አላቸው።

17. እነርሱም፣ “በዚህ ያለን አምስት እንጀራና ሁለት ዓሣ ብቻ ነው” አሉት።

18. እርሱም፣ “እስቲ ያለውን ወደ እኔ አምጡት” አላቸው።

ማቴዎስ 14