ማርቆስ 2:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኢየሱስ ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ቅፍርናሆም እንደ ተመለሰ፣ ወደ ቤት መግባቱን ሕዝቡ ሰማ።

2. ስለዚህ ከበሩ ውጭ እንኳ ሳይቀር ስፍራ እስኪታጣ ድረስ ብዙ ሕዝብ ተሰበሰበ፤ እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል ሰበከላቸው።

3. ጥቂት ሰዎችም አንድ ሽባ በአራት ሰዎች አሸክመው ወደ እርሱ አመጡ።

4. ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ኢየሱስ ወዳለበት መቅረብ ስላልቻሉ፣ የቤቱን ጣራ እርሱ ባለበት በኩል ነድለው ቀዳዳ በማበጀት ሽባው የተኛበትን ዐልጋ በዚያ አወረዱ።

5. ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፣ “አንተ ልጅ፣ ኀጢአትህ ተሰርዮልሃል!” አለው።

ማርቆስ 2