ማርቆስ 11:19-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. በመሸም ጊዜ ከከተማዪቱ ወጥተው ሄዱ።

20. በማግስቱ ጠዋት በመንገድ ሲያልፉ፣ በለሲቱ ከነሥሯ ደርቃ አዩ።

21. ጴጥሮስ ነገሩ ትዝ አለውና ኢየሱስን፣ “መምህር ሆይ፤ እነሆ፤ የረገምሃት በለስ ደርቃለች” አለው።

22. ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “በእግዚአብሔር እመኑ፤

23. እውነት እላችኋለሁ፤ ማንም ይህን ተራራ፣ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር’ ቢለውና ይህንንም በልቡ ሳይጠራጠር ቢያምን ይሆንለታል።

24. ስለዚህ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ እንደ ተቀበላችሁት አድርጋችሁ ብታምኑ ይሆንላችኋል።

ማርቆስ 11