ማርቆስ 1:36-39 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

36. ስምዖንና ባልደረቦቹም ተከትለው ይፈልጉት ጀመር፤

37. ባገኙትም ጊዜ፣ “ሰዉ ሁሉ ይፈልግሃል” አሉት።

38. እርሱም፣ “ከዚህ ተነሥተን በአቅራቢያ ወዳሉት መንደሮች እንሂድ፤ እዚያም ልስበክ፤ የመጣሁት ለዚሁ ነውና” አላቸው።

39. ስለዚህ ወደ ምኵራባቸው እየገባ በመስበክና አጋንንትን በማስወጣት በመላዋ ገሊላ ይዘዋወር ጀመር።

ማርቆስ 1