ማርቆስ 1:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የእግዚአብሔር ልጅ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ።

2. በነቢዩ በኢሳይያስ፣ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፤“እነሆ መንገድህን የሚያዘጋጅ መልእክተኛዬንበፊትህ እልካለሁ፤

3. ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ጥርጊያውንም አስተካክሉ እያለ በበረሓ የሚጮኽ ድምፅ’።”

4. ስለዚህ መጥምቁ ዮሐንስ በበረሓ እያጠመቀና ለኀጢአት ስርየት የንስሓ ጥምቀት እየሰበከ መጣ።

ማርቆስ 1