ማሕልየ መሓልይ 7:8-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. እኔም፣ “የዘንባባውን ዛፍ እወጣለሁ፤ዘለላዎቹንም እይዛለሁ” አልሁ።ጡቶችሽ የወይን ዘለላ፣የእስትንፋስሽም መዐዛ እንደ እንኰይ ፍሬ ይሁኑ፤

9. ከናፍሮችሽም እንደ ማለፊያ የወይን ጠጅ ይጣፍጡ።የወይን ጠጁ በቀስታ እየተንቈረቈረ፣ወደ ውዴ ከንፈሮችና ጥርሶች ይውረድ።

10. እኔ የውዴ ነኝ፤የእርሱም ምኞት እኔው ነኝ።

11. ውዴ ሆይ፤ ና ወደ ገጠር እንሂድ፤ወደ መንደርም ገብተን እንደር፤

12. ማልደን ወደ ወይኑ ተክል ቦታ እንሂድ፣ወይኑ እንቡጥ አውጥቶ፣አበባው ፈክቶ፣ሮማኑ አፍርቶ እንደሆነ እንይ፤በዚያም ራሴን በፍቅር እሰጥሃለሁ።

ማሕልየ መሓልይ 7