ማሕልየ መሓልይ 3:9-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ንጉሥ ሰሎሞን የራሱን ሠረገላ ሠራ፤የሠራውም ከሊባኖስ በመጣ ዕንጨት ነው።

10. ምሰሶዎቹን ከብር፣መደገፊያውንም ከወርቅ ሠራ፤መቀመጫውም በሐምራዊ ሐር የተሸፈነ ነው፤ውስጡም በኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፣አምሮ የተለበጠ ነው።

11. እናንት የጽዮን ቈነጃጅት ውጡ፤ንጉሥ ሰሎሞን አክሊሉን ደፍቶ እዩት፤ዘውዱም ልቡ ሐሤት ባደረገባት፣በዚያች በሰርጉ ዕለት፣እናቱ የደፋችለት ነው።

ማሕልየ መሓልይ 3