ሚክያስ 7:12-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. በዚያ ቀን ሰዎች፣ከአሦር እስከ ግብፅ ከተሞች፣ከግብፅ እስከ ኤፍራጥስ፣ከባሕር ወደ ባሕር፣ከተራራ ወደ ተራራ ወደ እናንተ ይመጣሉ።

13. ከሥራቸው የተነሣ፣በነዋሪዎቿ ምክንያት ምድር ባድማ ትሆናለች።

14. ብቻቸውን በዱር ውስጥ፣በለመለመ መስክ የሚኖሩትን፣የርስትህ መንጋ የሆኑትን፣ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፤እንደ ቀድሞው ዘመን፣በባሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።

15. “ከግብፅ እንደ ወጣህበት ዘመን ሁሉ፣ታምራቴን አሳያቸዋለሁ።”

16. አሕዛብ ያያሉ፣ ያፍራሉም፤ኀይላቸውን ሁሉ ያጣሉ፤አፋቸውን በእጃቸው ይይዛሉ፤ጆሮአቸውም ትደነቍራለች።

ሚክያስ 7