ሚክያስ 5:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አንቺ የጭፍሮች ከተማ ሆይ፤ጭፍሮችሽን አሰልፊ፤ከበባ ተደርጎብናልና፤የእስራኤልን ገዥ፣ጒንጩን በበትር ይመቱታል።

2. “አንቺ ግን፣ ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፤ከይሁዳ ነገዶች መካከል ትንሿ ብትሆኚም፣አመጣጡ ከጥንት፣ከቀድሞ ዘመን የሆነ፣የእስራኤል ገዥ፣ከአንቺ ይወጣልኛል።”

3. ስለዚህ ወላዲቱ አምጣ እስክትገላገል ድረስ፣እስራኤል ትተዋለች፤የተቀሩት ወንድሞቹም፣ተመልሰው ከእስራኤላውያን ጋር ይቀላቀላሉ።

4. በእግዚአብሔር ኀይልበአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ታላቅነት፣ጸንቶ ይቆማል፤ መንጋውንም ይጠብቃል።በዚያን ጊዜ ኀያልነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ስለሚደርስ፣ተደላድለው ይኖራሉ።

5. እርሱም ሰላማቸው ይሆናል።አሦራዊ ምድራችንን ሲወር፣ምሽጐቻችንንም ጥሶ ሲገባ፣ሰባት እረኞችን፣እንዲያውም ስምንት አለቆችን እናስነሣበታለን።

ሚክያስ 5