ሚክያስ 2:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ዕርሻ ይመኛሉ፤ ይይዙታልም፤ቤት ይመኛሉ፤ ይወስዱታልም፤የሰውን ቤት፣የባልንጀራን ርስት አታልለው ይወስዳሉ።

3. ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እነሆ፤ በዚያ ሕዝብ ላይ ጥፋት ላመጣ ዐቅጃለሁ፤ከዚህም ለማምለጥ አትችሉም።ከእንግዲህ በትዕቢት አትመላለሱም፤የመከራ ጊዜ ይሆናልና።

4. በዚያ ቀን ሰዎች ይሣለቁባችኋል፤በሐዘን እንጒርጒሮ እንዲህ እያሉ ያፌዙባችኋል፤‘እኛ ፈጽሞ ጠፍተናል፤የወገኔ ርስት ተከፋፍሎአል።ከእኔ ነጥቆ ወስዶ፣ዕርሻዎቻችንን ላሸነፉን አከፋፈለ።’

5. ስለዚህ በእግዚአብሔር ጉባኤ ውስጥ፣መሬት በዕጣ የሚያካፍል ማንም አይኖርም።

ሚክያስ 2