መዝሙር 98:2-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. እግዚአብሔር ማዳኑን አሳወቀ፤ጽድቁንም በሕዝቦች ፊት ገለጠ።

3. ለእስራኤል ቤት ምሕረቱን፣ታማኝነቱንም አሰበ፤የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ፣የአምላካችንን ማዳን አዩ።

4. ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤ውዳሴን አፍልቁ፤ በደስታና በዝማሬ አመስግኑ፤

5. ለእግዚአብሔር በገና ደርድሩለት፤በበገናና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩለት፤

6. በእንቢልታና በመለከት ድምፅ፣በንጉሡ በእግዚአብሔር ፊት እልል በሉ።

መዝሙር 98