መዝሙር 94:17-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. እግዚአብሔር ረዳቴ ባይሆን ኖሮ፣ነፍሴ ወደ ዝምታው ዓለም ፈጥና በወረደች ነበር።

18. እኔ፣ “እግሬ አዳለጠኝ” ባልሁ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ ደግፎ ያዘኝ።

19. የውስጤ ጭንቀት በበዛ መጠን፣ማጽናናትህ ነፍሴን ደስ አሰኛት።

20. ዐመፃን ሕጋዊ የሚያደርግ፣የጥፋት ዙፋን ከአንተ ጋር ሊያብር ይችላልን?

21. በጻድቁ ላይ ተሰልፈው ይወጣሉ፤በንጹሑም ላይ ሞት ይፈርዳሉ።

22. ለእኔ ግን እግዚአብሔር ምሽግ፣አምላኬም መጠጊያ ዐለት ሆኖኛል።

23. በደላቸውን ወደ ራሳቸው ይመልሳል፤በክፋታቸውም ያጠፋቸዋል፤ እግዚአብሔር አምላካችን ይደመስሳቸዋል።

መዝሙር 94