መዝሙር 90:5-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. እንደ ጐርፍ ጠርገህ ስትወስዳቸው፣ እንደ ሕልም ይበናሉ፤እንደ ማለዳ ሣር ታድሰው ይበቅላሉ፤

6. ሣሩም ንጋት ላይ አቈጥቍጦ ይለመልማል፤ምሽት ላይ ጠውልጎ ይደርቃል።

7. በቊጣህ አልቀናልና፤በመዓትህም ደንግጠናል።

8. በደላችንን በፊትህ፣የተሰወረ ኀጢአታችንንም በገጽህ ብርሃን ፊት አኖርህ።

9. ዘመናችን ሁሉ በቊጣህ ዐልፎአልና፤ዕድሜአችንንም በመቃተት እንጨርሳለን።

10. የዕድሜአችን ዘመን ሰባ ዓመት፣ ቢበዛም ሰማንያ ነው፤ከዚያ በላይ ከሆነም ድካምና መከራ ብቻ ነው፤ቶሎ ያልፋልና፤ እኛም ወዲያው እንነጒዳለን።

11. የቍጣህን ኀይል ማን ያውቃል?መዓትህም የመፈራትህን ያህል ታላቅ ነው።

መዝሙር 90