መዝሙር 90:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤አንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ መጠጊያችን ሆንህልን።

2. ገና ተራሮች ሳይወለዱ፣ምድርንና ዓለምን ከመፍጠርህ በፊት፣አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነህ።

3. ሰዎችን ወደ ዐፈር ትመልሳለህ፤“የሰው ልጆች ሆይ፤ ወደ ቦታችሁ ተመለሱ” ትላለህ፤

4. ሺህ ዓመት በፊትህ፣እንዳለፈችው እንደ ትናንት ቀን፣እንደ ሌሊትም እርቦ ነውና።

5. እንደ ጐርፍ ጠርገህ ስትወስዳቸው፣ እንደ ሕልም ይበናሉ፤እንደ ማለዳ ሣር ታድሰው ይበቅላሉ፤

6. ሣሩም ንጋት ላይ አቈጥቍጦ ይለመልማል፤ምሽት ላይ ጠውልጎ ይደርቃል።

7. በቊጣህ አልቀናልና፤በመዓትህም ደንግጠናል።

8. በደላችንን በፊትህ፣የተሰወረ ኀጢአታችንንም በገጽህ ብርሃን ፊት አኖርህ።

9. ዘመናችን ሁሉ በቊጣህ ዐልፎአልና፤ዕድሜአችንንም በመቃተት እንጨርሳለን።

መዝሙር 90