መዝሙር 89:42-46 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

42. የጠላቶቹን ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አደረግህ፤ባላንጣዎቹም ሁሉ ደስ አላቸው።

43. የሰይፉን ስለት አጠፍህ፤በጦርነትም ጊዜ አልረዳኸውም።

44. ግርማዊነቱን አጠፋህበት፤ዙፋኑንም ከዐፈር ደባለቅኸው።

45. የወጣትነት ዘመኑን አሳጠርኸው፤ዕፍረትንም አከናነብኸው። ሴላ

46. እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል? ራስህንስ ለዘላለም ትሰውራለህን?ቍጣህስ እንደ እሳት የሚነደው እስከ መቼ ነው?

መዝሙር 89