መዝሙር 89:40-44 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

40. ቅጥሩን ሁሉ አፈራረስህ፤ምሽጉንም ደመሰስህ።

41. ዐላፊ አግዳሚው ሁሉ ዘረፈው፤ለጎረቤቶቹ መዘባበቻ ሆነ።

42. የጠላቶቹን ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አደረግህ፤ባላንጣዎቹም ሁሉ ደስ አላቸው።

43. የሰይፉን ስለት አጠፍህ፤በጦርነትም ጊዜ አልረዳኸውም።

44. ግርማዊነቱን አጠፋህበት፤ዙፋኑንም ከዐፈር ደባለቅኸው።

መዝሙር 89