25. እጁን በባሕር ላይ፣ቀኝ እጁንም በወንዞች ላይ አኖራለሁ።
26. እርሱም፣ ‘አንተ አባቴ ነህ፤አምላኬና መዳኛ ዐለቴም ነህ’ ብሎ ይጠራኛል።
27. እኔም ደግሞ በኵሬ አደርገዋለሁ፤ከምድር ነገሥታትም በላይ ከፍ ይላል።
28. ምሕረቴንም ለዘላለም ለእርሱ እጠብቃለሁ፤ከእርሱ ጋር የገባሁት ኪዳንም ጸንቶ ይኖራል።
29. የዘር ሐረጉን ለዘላለም፣ዙፋኑንም በሰማያት ዕድሜ ልክ አጸናለሁ።
30. “ልጆቹ ሕጌን ቢተዉ፣ደንቤን ባይጠብቁ፣
31. ሥርዐቴን ቢጥሱ፣ትእዛዜንም ባያከብሩ፣
32. ኀጢአታቸውን በበትር፣በደላቸውን በጅራፍ እቀጣለሁ።
33. ምሕረቴን ግን ከእርሱ አላርቅም፤ታማኝነቴንም አላጓድልበትም።
34. ኪዳኔን አላፈርስም፤ከአፌ የወጣውንም አላጥፍም።