መዝሙር 89:20-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ባሪያዬን ዳዊትን አገኘሁት፤በተቀደሰው ዘይቴም ቀባሁት።

21. እጄ ይደግፈዋል፤ክንዴም ያበረታዋል።

22. በጠላት አይበለጥም፤ክፉ ሰውም አይበግረውም።

23. ባላንጣዎቹን በፊቱ አደቅቃቸዋለሁ፤ጠላቶቹንም እቀጠቅጣለሁ።

24. ታማኝነቴና ምሕረቴ ከእርሱጋር ይሆናል፤በስሜም ቀንዱ ከፍ ከፍ ይላል።

መዝሙር 89