መዝሙር 89:16-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. ቀኑን ሙሉ በስምህ ደስ ይላቸዋል፤በጽድቅህም ሐሤት ያደርጋሉ፤

17. አንተ የብርታታቸው ክብር ነህና፤በሞገስህም ቀንዳችንን ከፍ ከፍ አደረግህ።

18. ጋሻችን የእግዚአብሔር ነውና፤ንጉሣችንም የራሱ የእስራኤል ቅዱስ ነው።

19. በዚያን ጊዜ በራእይ ተናገርህ፤ታማኝ ሕዝብህንም እንዲህ አልህ፤“ኀያሉን ሰው ሥልጣን አጐናጸፍሁት፤ከሕዝብ መካከል የተመረጠውንም ከፍ ከፍ አደረግሁት።

20. ባሪያዬን ዳዊትን አገኘሁት፤በተቀደሰው ዘይቴም ቀባሁት።

መዝሙር 89