መዝሙር 85:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምድርህ በጎ ውለሃል፤የያዕቆብንም ምርኮ መለስህ።

2. የሕዝብህን በደል ይቅር አልህ፤ኀጢአታቸውንም ሁሉ ሸፈንህ። ሴላ

3. መዓትህን ሁሉ አራቅህ፤ከብርቱ ቍጣህም ተመለስህ።

4. መድኀኒታችን የሆንህ አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤በእኛ ላይ የተቃጣውን ቍጣህን መልሰው።

5. የምትቈጣን ለዘላለም ነውን?ቊጣህስ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይቀጥላልን?

መዝሙር 85