መዝሙር 84:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ንጉሤና አምላኬ የሰራዊት አምላክ ሆይ፤መሠዊያህ ባለበት ስፍራ፣ድንቢጥ እንኳ መኖሪያ ቤት፣ዋኖስም ጫጩቶቿን የምታኖርበት ጐጆ አገኘች።

4. በቤትህ የሚኖሩ የተባረኩ ናቸው፤እነርሱም ለዘላለም ያመሰግኑሃል። ሴላ

5. አንተን ብርታታቸው ያደረጉ፣በልባቸው የጽዮንን መንገድ የሚያስቡ ቡሩካን ናቸው።

6. በልቅሶ ሸለቆ በሚያልፉበት ጊዜ፣የምንጭ መፍለቂያ ቦታ ያደርጉታል፤የበልጒም ዝናብ ያረሰርሰዋል።

መዝሙር 84