1. የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ማደሪያህ ምንኛ የተወደደ ነው!
2. ነፍሴ የእግዚአብሔርን አደባባዮች ትናፍቃለች፤እጅግም ትጓጓለታለች፤ልቤና ሥጋዬም፣ለሕያው አምላክ እልል በሉ።
3. ንጉሤና አምላኬ የሰራዊት አምላክ ሆይ፤መሠዊያህ ባለበት ስፍራ፣ድንቢጥ እንኳ መኖሪያ ቤት፣ዋኖስም ጫጩቶቿን የምታኖርበት ጐጆ አገኘች።
4. በቤትህ የሚኖሩ የተባረኩ ናቸው፤እነርሱም ለዘላለም ያመሰግኑሃል። ሴላ
5. አንተን ብርታታቸው ያደረጉ፣በልባቸው የጽዮንን መንገድ የሚያስቡ ቡሩካን ናቸው።
6. በልቅሶ ሸለቆ በሚያልፉበት ጊዜ፣የምንጭ መፍለቂያ ቦታ ያደርጉታል፤የበልጒም ዝናብ ያረሰርሰዋል።