መዝሙር 83:4-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. “የእስራኤል ስም ከእንግዲህ እንዳይታወስ፣ኑና ሕዝብ እንዳይሆኑ እንደምስሳቸው” አሉ።

5. በአንድ ሐሳብ ተስማምተው ተማከሩ፤በአንተም ላይ ተማማሉ፤

6. የኤዶምና የእስማኤላውያን ድንኳኖች፣የሞዓብና የአጋራውያን ድንኳኖች፣

7. ጌባል፣ አሞንና አማሌቅ፣ፍልስጥኤምም ከጢሮስ ሕዝብ ጋር ሆነው ዶለቱ፤

8. አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፤የሎጥ ልጆችም ረዳት ሆነ። ሴላ

9. በምድያም ላይ እንዳደረግኸው አድርግባቸው፤በቂሶንም ወንዝ በሲሣራና በኢያቢስ ላይ ያደረስኸው ይድረስባቸው።

መዝሙር 83