መዝሙር 83:4-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. “የእስራኤል ስም ከእንግዲህ እንዳይታወስ፣ኑና ሕዝብ እንዳይሆኑ እንደምስሳቸው” አሉ።

5. በአንድ ሐሳብ ተስማምተው ተማከሩ፤በአንተም ላይ ተማማሉ፤

6. የኤዶምና የእስማኤላውያን ድንኳኖች፣የሞዓብና የአጋራውያን ድንኳኖች፣

7. ጌባል፣ አሞንና አማሌቅ፣ፍልስጥኤምም ከጢሮስ ሕዝብ ጋር ሆነው ዶለቱ፤

8. አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፤የሎጥ ልጆችም ረዳት ሆነ። ሴላ

9. በምድያም ላይ እንዳደረግኸው አድርግባቸው፤በቂሶንም ወንዝ በሲሣራና በኢያቢስ ላይ ያደረስኸው ይድረስባቸው።

10. እነርሱም በዐይንዶር ጠፉ፤እንደ ምድርም ጒድፍ ሆኑ።

11. መኳንንታቸውን እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፣መሳፍንታቸውንም ሁሉ እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው፤

12. እነዚህም፣ “የእግዚአብሔርን የግጦሽ ቦታ፣ወስደን የግላችን እናድርግ” የሚሉ ናቸው።

13. አምላኬ ሆይ፤ በዐውሎ ነፋስ እንደሚነዳ ትቢያ፣በነፋስም ፊት እንዳለ ገለባ አድርጋቸው።

መዝሙር 83