መዝሙር 83:13-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. አምላኬ ሆይ፤ በዐውሎ ነፋስ እንደሚነዳ ትቢያ፣በነፋስም ፊት እንዳለ ገለባ አድርጋቸው።

14. እሳት ደንን እንደሚያጋይ፣ነበልባልም ተራራን እንደሚያቃጥል፣

15. እንዲሁ በሞገድህ አሳዳቸው፤በማዕበልህም አስደንግጣቸው።

16. እግዚአብሔር ሆይ፤ ስምህን ይሹ ዘንድ፣ፊታቸውን በዕፍረት ሙላው፤

17. ለዘላለም ይፈሩ፤ ይታወኩም፤በውርደትም ይጥፉ።

18. ስምህ እግዚአብሔር የሆነው አንተ ብቻ፣በምድር ሁሉ ላይ ልዑል እንደሆንህ ይወቁ።

መዝሙር 83