መዝሙር 83:10-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. እነርሱም በዐይንዶር ጠፉ፤እንደ ምድርም ጒድፍ ሆኑ።

11. መኳንንታቸውን እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፣መሳፍንታቸውንም ሁሉ እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው፤

12. እነዚህም፣ “የእግዚአብሔርን የግጦሽ ቦታ፣ወስደን የግላችን እናድርግ” የሚሉ ናቸው።

13. አምላኬ ሆይ፤ በዐውሎ ነፋስ እንደሚነዳ ትቢያ፣በነፋስም ፊት እንዳለ ገለባ አድርጋቸው።

መዝሙር 83