1. አምላክ ሆይ፤ ዝም አትበል፤አምላክ ሆይ፤ ጸጥ አትበል፤ ጭጭ አትበል።
2. ጠላቶችህ እንዴት እንደ ተነሣሡ፣ባላንጣዎችህም እንዴት ራሳቸውን ቀና ቀና እንዳደረጉ ተመልከት።
3. በሕዝብህ ላይ በተንኰል አሤሩ፤በውድ ልጆችህ ላይ በአንድነት ተመካከሩ።
4. “የእስራኤል ስም ከእንግዲህ እንዳይታወስ፣ኑና ሕዝብ እንዳይሆኑ እንደምስሳቸው” አሉ።
5. በአንድ ሐሳብ ተስማምተው ተማከሩ፤በአንተም ላይ ተማማሉ፤
6. የኤዶምና የእስማኤላውያን ድንኳኖች፣የሞዓብና የአጋራውያን ድንኳኖች፣
7. ጌባል፣ አሞንና አማሌቅ፣ፍልስጥኤምም ከጢሮስ ሕዝብ ጋር ሆነው ዶለቱ፤